am_tn/isa/17/08.md

1.7 KiB

ወደ መሠዊያቸው አይመለከቱም

ወደ መሠዊያ መመልከት ጣዖቶቹ ይረዱናል በሚል ተስፋ ጣዖቶችን ማምለክን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መሠዊያቸው ላይ ጣዖቶችን አያመልኩም›› ወይም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ ወደ መሠዊያቸው ሄደው እንዲረዷቸው አማልክቶቻችውን አይለምኑም››

በእጃቸው ወደ ሠሯቸው

መሠዊያዎቹን ወይም ጣዖቶቹን የሠሯቸው እነርሱ መሆናቸውን አጽንዖት ለመስጠት እዚህ ላይ ሰዎች ‹‹በእጃቸው›› ተወክለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእጆቻቸው የሠሯቸው›› ወይም፣ ‹‹ራሳቸው የሠሩትን››

በጣቶቻቸው ላበጇቸው… የአሼራ ዐምዶች ወይም የፀሐይ ምስሎች

ሁለተኛው ሐረግ ሰዎቹ የሠሩትን ያመለክታል፡፡ ስለ ጣቶች የተነገረው ሰዎች እንዳበጇቸውና ስለዚህ እነዚህ እውነተኛ አማልክት አለመሆናቸውን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነርሱ ራሳቸው ላበጇቸው የአሼራ ዐምዶች ወይም የፀሐይ ምስሎች››

በእስራኤል ልጆች ምክንያት የተተውት

እነዚህን ምድሮች የተውት እነማን እንደ ነበሩ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ሕዝብ ከመጡ በኃላ ኬጢያውያንና አሞራውያን ትተው ሄዱ››