am_tn/isa/17/06.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የእስራኤልን ሕዝብ መከር ከታጨደ በኃላ ካለው እርሻ ጋር ማመሳሰሉን ቀጥሏል፡፡ (ኢሳይያስ 17፥4-5 ይመ.)

ቃርሚያ ይተርፋል

እዚያ ላይ፣ ‹‹ቃርሚያ›› በእስራኤል የቀረውን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእስራኤል ጥቂት ሰዎች ይቀራሉ››

የወይራ ዛፍ በተናወጠ ጊዜ

ሰዎች የወይራ ፍሬ የሚሰበሰቡት ፍሬው እንዲረግፍ ዛፉን በመነቅነቅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ከሰበሰቡ በኃላ ዛፉ ላይ እንደሚቀር ጥቂት የወይራ ፍሬ››

አራት ወይም አምስት

ከዚህ በፊት ከነበረው ቁጥር ‹‹የወይራ ፍሬ›› የሚለው ቃል ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አራት ወይም አምስት ፍሬ››

ይላል የእስራኤል አምላክ ያህዌ

እየተናገረ ያለውን እርግጠኝነት ለማመልከት ያህዌ ስሙን በመጥራት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ የእስራኤል አምላክ ያህዌ የተናገረው ነው›› ወይም፣ ‹‹ይህ እኔ የእስራኤል አምላክ ያህዌ የተናገርሁት ነው››

ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ… ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ

እዚህ ላይ ወደ እግዚአብሔር መመልከት እንደሚረዳቸው በእርሱ ተስፋ ማድረግን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች የፈጠራቸው የእስራኤል ቅዱስ እንደሚረዳቸው ተስፋ ያደርጋሉ››

ሰዎች ይመለከታሉ

‹‹ሰዎች›› በጠቅላላው የእስራኤል ሕዝብ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ያያሉ››

ዐይኖቻቸው ያያሉ

‹‹ዐይኖች›› የሚመለከቱ ሰዎችን ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያያሉ›› ወይም፣ ‹‹ሕዝቡ ያያሉ››

የእስራኤል ቅዱስ

ኢሳይያስ 1፥4 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡