am_tn/isa/17/01.md

2.6 KiB

ስለ ደማስቆ

ደማስቆ የከተማ ስም ነው፡፡ ኢሳይያስ 7፥8 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ ‹‹ሰዎች ሁሉ የአሮኤርን ከተማ ትተው ይሄዳሉ››

ማንም አያስፈራቸውም

‹‹እነርሱ›› የሚለው የሚያመለክተው በጐቹን ነው፡፡

የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም ይጠፋሉ

ኤፍሬም በእስራኤል ትልቁ ነገድ ነበር፡፡ እዚህ ላይ መላው የእስራኤልን ሰሜናዊ መንግሥት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእስራኤል ጠንካራ ከተሞች ይጠፋሉ››

ይጠፋሉ

ይህ ማለት ብን ብለው ይጠፋሉ ሳይሆን፣ ይደመሰሳሉ ማለት ነው፡፡

ከደማስቆ መንግሥት

‹‹ይጠፋሉ›› ቀደም ሲል ከነበረው ቁጥር ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ ደማስቆ የሶርያ ንጉሥ የሚገዛበት ቦታ ነበረች፡፡ መንግሥቱ መጥፋቱ ከእንግዲህ እንደ ንጉሥ የመግዛት ሥልጣን እንደማይኖረው ነው የሚያመላክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከደማስቆ መንግሥት ይጠፋል›› ወይም፣ ‹‹በደማስቆ የንጉሥ ሥልጣን አይኖርም››

ሶርያ

ሶርያ የአገር ስም ነው፡፡ ኢሳይያስ 7፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

እንደ እስራኤል ሕዝብ ክብር ይሆናሉ

የእስራኤል ሕዝብ ምንም ክብር እንዳልነበራቸው ሁሉ፣ ከሶርያ የተረፉትም ምንም ክብር አይኖራቸውም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ እንደ እስራኤል ሕዝብ እነርሱም ምንም ክብር አይኖራቸውም›› ወይም፣ ‹‹በእስራኤል ሕዝብ እንዳደረግሁ እነርሱም ላይ እፍረት አመጣለሁ››

የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

የሚናገረውን ነገር እርግጠኝነት ለማመልከት ያህዌ ስሙን በመጥራት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ኢሳይያስ 14፥22 ላይ እንደ ተረጐምህ ተርጉመው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰራዊት ጌታ ያህዌ የሚለው ይህን ነው›› ወይም፣ ‹‹እኔ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ይህን ብያለሁ››