am_tn/isa/16/11.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ስለ ሞዓብ ሕዝብ የተነገረው ትንቢት ቀጣይ ነው፡፡ ወደ ፊት የሚሆን ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተፈጸሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)፡፡

ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ በገና የሐዘን እንጉርጉሮ ታሰማለች

‹‹ልቤ›› የሚለው ያህዌንና ያዘነ ስሜቱን ይወክላል፡፡ የእርሱን እንጉርጉሮ ከአሳዛኝ የበገና ዜማ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ በበገና እንደሚሰማው የሐዘን ዜማ አንጐራጉራለሁ››

ሞዓብ… እርሱ ራሱ… የእርሱ

እነዚህ ቃላት ሁሉ የሞዓብን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡

ውስጤ ስለ ቂርሐራሴት

‹‹ውስጤ›› የሚለው ቃል ያህዌን ያመለክታል፡፡ ‹‹እንጉርጉሮ›› የሚለው ካለፈው ሐረግ ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ ኢሳይያስ 16፥7 ላይ ቂርሐራሴትን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ውስጤ ስለ ቂርሐራሴት ታንጐራጉራለች›› ወይም፣ ‹‹ለቂርሐራሴት ሰዎች በጣም አዝኛለሁ››

ጸሎቱ ምንም አያደርግም

‹‹ጸሎቱ መልስ አያገኝም››