am_tn/isa/16/06.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ስለ ሞዓብ የተነገረው ትንቢት ቀጣይ ነው፡፡ ወደ ፊት የሚደረጉ ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተደረጉ ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)

የሞዓብን ትዕቢት፣ እብሪቱን፣ የእርሱን ፉከራና ቁጣውን ሰምተናል፡፡

‹‹ሞዓብ›› እና፣ ‹‹የእርሱ›› የሚሉት ቃሎች፣ የሞዓብን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ የሞዓብ ሕዝብ ትዕቢተኞች፣ እብሪተኞች፣ ፎካሪችና ቁጣዎች መሆናቸውን ሰምተናል››

ሰምተናል

ይህም ማለት፣ 1) ኢሳይያስ እየተናገረ ነው፤ ‹‹እኛ›› እርሱንና የይሁዳን ሕዝብ የሚያመላክት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም፣ 2) እየተናገረ ያለው እግዚአብሔር ነው፤ ‹‹እኛ›› የሚለው እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡

ትዕቢቶቹ ግን ከንቱ ቃላት ናቸው

‹‹አንዳች ነገርን አስመልክቶ የሚናገሩት ከንቱ ነው›› ወይም፣ ‹‹የሚታበዩበት ነገር እውነት አይደለም››

ስለዚህ ሞዓብ ለሞዓብ ዋይ ይላል - ሁሉም ዋይ ይላሉ

‹‹ሞዓብ›› የሚወክለው የሞዓብን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹የሞዓብ ሕዝብ ሁሉ ከተሞቻቸው ላይ ከሆነው የተነሣ ዋይ ይላሉ››

ስለ ቂርሐራሴት የዘቢብ ቂጣ

‹‹በቂርሐራሴት የዘቢብ ቂጣ ስለሌለ››

የዘቢብ ቂጣ

እዚህ ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራይስጥ ቃል፣ ‹‹የዘቢብ ቂጣ›› ወይም፣ ‹‹ሰዎች›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ቂርሐራሴት

ቂርሐራሴት የከተማ ስም ነው፡፡