am_tn/isa/16/05.md

941 B

በኪዳን ታማኝነት ዙፋን ይመሠረታል

‹‹ዙፋን›› እንደ ንጉሥ የመግዛትን ሥልጣን ያመለክታል፡፡ ‹‹ታማኝነት›› የሚለውን ‹‹ታማኝ›› ማለት ይቻላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ለኪዳኑ ታማኝ ይሆናል፤ እርሱም ንጉሥ ይሾማል››

ከዳዊት ድንኳን የሆነውም በዚያ ላይ በታማኝነት ይቀመጣል

‹‹የዳዊት ድንኳን›› ዘሮቹን ጨምሮ የዳዊትን ቤተ ሰብ ይወክላል፡፡ ዙፋን ላይ መቀመጥ መግዛትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዳዊት ዘር በታማኝነት ይገዛል››

ፍትሕን ይፈልጋል

ፍትሕ መፈለግ ትክክል የሆነውን ማድረግን ያመለክታል፡፡