am_tn/isa/16/03.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ስለ ሞዓብ የተነገረው ትንቢት ቀጥሏል፡፡ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተደረጉ አድርጐ ይናገራል፡፡ ከቁጥር 3-4 ያለው የሞዓብ ገዦች ለይሁዳ ንጉሥ የላኩት መልእክት ሊሆን ይችላል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)፡፡

በቀትር ጥላችሁን እንደ ሌሊት አጥሉብን

እኩለ ቀን ላይ ያለው ሙቀት ሞዓባውያን በጠላቶቻቸው የሚደርስባቸውን መከራ ያመለክታል፤ ጥላ ከጠላቶቻቸው መከለያን ያመለክታል፡፡ ጥላውን ከሌሊት ጋር ማመሳሰሉ ጠንካራ መከለያ እንደሚያስፈልጋቸው ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታላቅ ጥላ ሕዝቡን ከፀሐይ ሙቀት እንደሚከላከል እናንተም ከጠላቶቻችን ከለሉን››

የሞዓብ ስደተኞች በመካከላችሁ ይኑሩ

‹‹የሞዓብ ስደተኞች ከእናንተ ጋር ይኑሩ›› እዚህ ላይ፣ ‹‹እናንተ›› የሚያመለክተው የይሁዳን ሕዝብ ነው፡፡

ከአጥፊው መደበቂያ ቦታ ሁኑላቸው

መደበቂያ ቦታ ማዘጋጀት መደበቂያ ቦታ መሆን ተደርጐ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሊያጠፏቸው ከሚፈልጉ የሚደበቁበት ቦታ ስጧቸው›› ወይም፣ ‹‹ሊያጠፏቸው ከሚፈልጉ ደብቋቸው››