am_tn/isa/16/01.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ስለ ሞዓብ ሕዝብ የተነገረው ትንቢት እየቀጠለ ነው፡፡ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተደረጉ አድርጐ ይናገራል፡፡ ቁጥር አንድ የሞዓብ ገዦች እርስ በርስ የሚነጋገሩትን በተመለከተ እግዚአብሔር የተናገረው ሊሆን ይችላል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)

ለምድሪቱ ገዥ የበግ ጠቦት ላኩ

ከጠላት ሰራዊት እንዲከላከልላቸው ሞዓባውያን ለይሁዳ ንጉሥ የበግ ጠቦት ይልካሉ፡፡

ሴላ

ይህ የከተማ ስም ነው፡፡

የጽዮን ሴት ልጅ

የከተማው፣ ‹‹ሴት ልጅ›› ማለት የከተማው ሕዝብ ማለት ነው፡፡ ኢሳይያስ 1፥8 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ ‹‹የጽዮን ሕዝብ›› ወይም፣ ‹‹በጽዮን የሚኖር ሕዝብ››

እንደ ተቅበዝባዥ ወፎች፣ እንደ ተበተኑ ጐጆዎች የሞዓብ ሴቶችም በአርኖን ወንዝ መሻገሪያ እንዲሁ ይሆናሉ

ሴቶቹን ጨምሮ የሞዓብ ሕዝብ ሁሉ ከቤታቸው ይሸሻሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሞዓብ ሴቶች ጐጆ እንደሌላቸው በጐች ከአንዱ ወንዝ ወደ ሌላው ወንዝ ይቅበዘበዛሉ››

እንደ ተቅበዝባዥ ወፎች፣ እንደ ተበተኑ ጐጆዎች

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ አንድ ነገር ማለት ናቸው፡፡