am_tn/isa/15/08.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ስለ ሞዓብ ሕዝብ የተነገረው ትንቢት ቀጥሏል፡፡ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተነገሩ አድርጐ ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)

ጩኸታቸው ወደ ሞዓብ ዳርቻ ወጣ

ሰዎቹ ሲጮኹ ሌሎች ያንን መስማታቸው የጩኸታቸው መውጣት እንደሆነ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሞዓብ ምድር ያሉ ሰዎች ሁሉ ጮኹ››

ዋይታቸው እስከ ዔግሌምና ብኤር ኢላም

‹‹ወጣ›› ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ ሰዎች ዋይ ሲሉ ሌሎች ያንን መስማታቸው ዋይታቸው ወደ እነዚህ ሁለት ቦታዎች ወጣ ማለት እንደሆነ ተነግሮአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዋይታቸው እስከ ዔግላምና ብኤርኢላም ወጣ›› ወይም፣ ‹‹እስከ ዔግራምና ብኤርኤላም እንኳ ወጣ››

ዔግላም… ብኤርኤላም.. ዲሞን

እነዚህ የከተማና የመንደር ስሞች ናቸው፡፡ ዲሞን የሞዓብ አገር ዋና ከተማ ነበረች፡፡ አንዳንድ ቅጂዎች ከዲሞን ይልቅ፣ ‹‹ዶቦን›› ይላሉ፡፡

በዲሞን ላይ ግን ከዚያ የበለጠ ነገር አደርጋለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እኔ›› ያህዌን፣ ‹‹ዲሞን›› ደግሞ እዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዲሞን ሕዝብ ላይ የባሰ መከራ አመጣለሁ››