am_tn/isa/15/05.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ስለ ሞዓብ የተነገረው ትንቢት እየቀጠለ መሆኑን ያሳያል፡፡ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተደረጉ አድርጐ ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)

ልቤ ለሞዓብ ያለቅሳል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ልብ›› የሚወክለው እግዚአብሔርን ሲሆን፣ ስሜቱን ያመለክታል፡፡ ልቡ ያለቀሰ ይመስል እግዚአብሔር የተሰማውን ታላቅ ሐዘን እየተናገረ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሞዓብ ላይ በሆነው እጅግ አዝኛለሁ››

ስደተኞቿም ሸሹ

‹‹ስደተኞቹ ከሞዓብ ሸሹ›› ስደተኛ ጠላት እንዳይዘው የሚሸሽ ሰው ነው፡፡

ዞዓር… ዔግላት ሺሊሺያ… ሉሒት… ሐሮናይም… ኒምሪም

እነዚህ የከተሞችና የመንደሮች ስም ናቸው

ስለ ውድመታቸው

‹‹ውድመት›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹መደምሰስ›› በሚለው ቃል ለመተካት ቃላቱን መለወጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከተማቸው ስለ ተደመሰሰች››

ያከማቹት

‹‹ማንኛውም ነገራቸው››

የዲሞን ወንዞች

ይህ የሚያመለክተው ደቡባዊ የሞዓብ ድንበር ላይ ያለውን ወንዝ ሊሆን ይችላል፡፡