am_tn/isa/15/03.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እዚህም ላይ ስለ ሞዓብ ሕዝብ የተነገረው ትንቢት ቀጥሏል፡፡ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮችን እግዚአብሔር አሁን እንደ ተፈጸሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ (ኢሳይያስ 15፥1-2 ይመ.)

ማቅ ይለብሳሉ

እንዲህ የሚያደርጉት በጣም ማዘናቸውን ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማቅ ለብሰው ያለቅሳሉ››

ሐሴቦን… ኤልያሉ… ያሁድ

እነዚህ የከተሞችና የመንደሮች ስም ናቸው

ሐሴቦንና ኤልያሊ ይጣራሉ

የከተሞቹ ስሞች በውስጣቸው ያለውን ሕዝብ ይወክላሉ፡፡ ‹‹የሐሴቦንና የኤልያሊ ሕዝብ ይጣራሉ››

ይርዳሉ፤ ይንቀጠቀጣሉ

መንቀጥቀጥ የፍርሃት ምልክት ሲሆን፣ ፍርሃትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከባድ ፍርሃት ይሞላባቸዋል›› ወይም፣ ‹‹በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ››