am_tn/isa/15/01.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ብዙውን ጊዜ ትንቢት ውስጥ ወደ ፊት የሚፈጸሙ ጉዳዮች አሁን ወይም ባለፈው ጊዜ እንደ ተፈጸሙ ተደርገው ይነገራሉ፡፡ ይህ አጽንዖት የሚሰጠው በእርግጥ የሚፈጸም መሆኑን ነው፡፡

የንግር ቃል

‹‹ያህዌ እንዲህ ይላል›› ወይም፣ ‹‹ይህ የያህዌ መልእክት ነው››

ዔር… ቂር… ዲቦን… ናባው… ሜድባ

እነዚህ ሞዓብ ውስጥ የነበሩ ከተሞችና መንደሮች ናቸው፡፡

የሞዓብ ዔር ፈራረሰች ተደመሰሰች

‹‹ፈራረሰች›› እና፣ ‹‹ተደመሰሰች›› የተሰኙት ቃሎች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፤ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንደምትደመሰስ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጠላት ሰራዊት የሞዓብን ዔር ሙሉ በሙሉ ይደመስሳታል››

ሊያለቅስም ወደ ከፍታዎች ሄደ

እነዚህ ላይ፣ ‹‹ወደ ከፍታዎች›› ሲል ቤተ መቅደስ ወይም መሠዊያ የተሠራበት ኮረብታ ወይም ተራራ የመሳሰሉ ከፍታ ቦታዎችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለማልቀስ ኮረብታው ጫፍ ላይ ወዳለው ቤተ መቅደስ ሄደ››

ሞዓብ ስለ ናባው እና ስለ ሜድባ አለቀሰ

እነዚህ ቦታዎች እዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ናባው እና ሜድባ ከተማ ላይ ከደረሰው የተነሣ የሞዓብ ሕዝብ ያለቅሳል››

ራሳቸውን ሁሉ ተላጭተዋል፤ ጢማቸውን ሁሉ ተላጭተዋል

እንዲህ ያደረጉት በጣም ማዘናቸውን ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሳቸውንና ጢማቸውን ሁሉ ተላጭተው በጣም ያዝናሉ››