am_tn/isa/14/31.md

2.0 KiB

ዋይ በል፣ በር፣ ጩኽ፣ ከተማ

‹‹በር›› እና፣ ‹‹ከተማ›› በከተሞች በር የሚቀመጡ ሰዎችን ይወክላል፡፡ ‹‹በከተማው በሮች ያላችሁ ሰዎች ዋይ በሉ፤ በከተሞቹም ያላችሁ ጩኹ››

ትቀልጣላችሁ

መቅለጥ ከፍርሃት የተነሣ ደካማ መሆንን ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከፍርሃት የተነሣ በጣም ትደክማላችሁ››

የጢስ ደመና ከሰሜን መጥቶብሃል

ይህ የሚያመለክተው ግዙፍ ሰራዊት ከሰሜን እየመጣ መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከጢስ ደመና ጋር ከሰሜን ብዙ ሰራዊት መጥቶብሃል››

የጢስ ደመና

ይህም ማለት፣ 1) በደረቁ ዐፈር ላይ ሲጓዝ ሰራዊቱ የሚያስነሣውን የአቧራ ደመና ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአቧራ ደመና›› ወይም 2) ሰራዊቱ ከሚያጠፋውና ከሚያቃጥለው ነገር የተነሣ ብዙ ጢስ ሊኖር ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙ ጢስ››

ከሰልፉ ተነጥሎ የሚቀር የለም

‹‹ከሰልፉ ከሌሎች ኃላ በዝግታ የሚራመድ አይኖርም››

ለዚያ ሕዝብ መልእክተኞች ምን መልስ ይሰጣሉ?

ጸሐፊው ይህን ጥያቄ ያነሣው እስራኤላውያን ለመልእክተኞቹ እንዴት መናገር እንዳለባቸው የሚያቀርበውን መመሪያ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለፍልስጥኤም መልእክተኞች እንዲህ በሏቸው››

ያህዌ ጽዮንን መሥርቶአታል

‹‹ያህዌ ጽዮንን ሠርቷል››

በእርሷ

‹‹በኢየሩሳሌም›› ወይም፣ ‹‹በዚያ››

ከሕዝቡ በጣም የተጐዱት

‹‹ከሕዝቡ በጣም የተጐዱ ሰዎች››