am_tn/isa/14/28.md

1.7 KiB

የመታህ በትር ተሰብሮአል

ፍልስጥኤምን የመታ በትር እነርሱን እንዲያጠቃ ሰራዊቱን የላከውን ንጉሥ ይወክላል፡፡ መሰበር መሞት ወይም መሸነፍን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰራዊቱን ወደ አንተ የላከው ንጉሥ ሞቶአል›› ወይም፣ ‹‹አንተን ያጠቃ ሰራዊት ተሸንፎአል››

ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣል… ዘሩም በራሪ እሳት ይሆናል

እነዚህ ሁሉ ሐረጐች የሚያመለክቱት የእባቡ ዘር ከራሱ ከእባቡ የባሰ ጐጂ መሆኑን ነው፡፡ የንጉሡ ወራሽ ከመጀመሪያው ንጉሥ የበለጠ ኀይለኛና ጨካኝ እንደሚሆን ያመለክታሉ፡፡

እፉኝት

የአደገኛ እባብ ዐይነት

እሳታማ በራሪ እባብ

‹‹እሳታማ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእባቡን መርዘኛነት ሲሆን፣ ‹‹በራሪ›› የሚለው ፈጣን እንቅስቃሴውን ሊያመለክት ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፈጣን መርዘኛ እባብ››

የድኻ በኩር

ይህ የሚያመለክተው በጣም ድኻ የሆኑ ሰዎችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከድኻም ድኻ›› ወይም፣ ‹‹የሕዝቤ የባሰባቸው ድኾች››

ሥርህን በራብ እገድላለሁ፤ ትሩፍህንም እፈጃለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሥርህ›› የፍልስጥኤምን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝብህን በራብ እገድላለሁ፤ ትሩፍህንም እጨርሳለሁ››