am_tn/isa/14/26.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እየተናገረ ያለው ኢሳይያስ ይሆናል ወይም ያህዌ ይሆናል

ለምድር ሁሉ የታቀደው ይህ ነው

‹‹የታቀደው›› የሚለውን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለምድር ሁሉ እግዚአብሔር ያለው ዕቅድ ይህ ነው››

በአሕዛብ ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይህ ነው

እግዚአብሔር አሕዛብን ለመቅጣት መዘጋጀቱ እነርሱን ለመምታት እጁን ከመዘርጋት ጋር ተመሳስሎአል፡፡ ‹‹እጅ›› የሚለው ቃል ኀይሉን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ አሕዛብን ሁሉ የሚቀጣ የያህዌ ኀይል ነው›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ አሕዛብን የሚቀጣው እንዲህ ነው››

ማን ያስቆመዋል?

ጥያቄው ያህዌን ማንም እንደማያስቆመው አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚያስቆመው የለም››

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

እጁም ተዘርግቷል

ይህ ያህዌ አሕዛብን ለመቅጣት መዘጋጀቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነርሱን›› ለመቅጣት ተዘጋጅቶአል››

ማንስ ይመልሰዋል?

ጥያቄው የቀረበው የእግዚአብሔርን እጅ የሚመልሰው እንደሌለ ለመናገር ነው፡፡ የእርሱን እጅ መመለስ አሕዛብን እንዳይቀጣ እርሱን ማስቆም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም›› አይመልሰውም›› ወይም፣ ‹‹እነርሱን እንዳይቀጣ ማንም አይመልሰውም››