am_tn/isa/14/24.md

2.1 KiB

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

እንደ ዐቀድሁት እንዲሁ ይሆናል፤ እንደ አሰብሁት ይከናወናል

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ያቀድሁት ነገር በእርግጥ ይሆናል››

አሦራውያንን በእጄ ላይ እሰብራለሁ

መስበር የሚወክለው ማሸነፍን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሦራውያንን በምድሬ ላይ አሸንፋቸዋለሁ›› ወይም፣ ‹‹በምድሬ ያሉትን አሦራውያን አሸንፋቸዋለሁ››

አሦራውያን

ይህ የሚወክለው የአሦራውያንን ንጉሥና ሰራዊቱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአሦራውያን ንጉሥና ሰራዊቱ›› ወይም፣ ‹‹የአሦራውያን ሰራዊት››

በእግሬ እረግጠዋለሁ

ይህ የሚያመለክተው ጨርሶ ማሸነፍን ነው፡፡

በዚያ ጊዜ ቀንበሩ ከላያቸው፣ ሸክሙም ከትከሻቸው ይነሣል

ይህ በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚያ ጊዜ ቀንበሩን ከላያቸው ሸክሙንም ከትከሻው አነሣለሁ፡፡

በዚያ ጊዜ ቀንበሩ ከላያቸው፣ ሸክሙም ከትከሻቸው ይነሣል

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ቀንበርንና ሸክምን ማንሣት ሰዎችን ከባርነት ነጻ ማድረግ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በዚያ ጊዜ ከባዱን ሸክም ከትከሻቸው በማስወገድ እስራኤላውያንን ከአሦራውያን ባርነት ነጻ አደርጋለሁ››

ቀንበሩ… ሸክሙ

‹‹የእርሱ›› የሚለው የሚያመለክተው አሦርን ነው፡፡

ከላያቸው… ከትከሻቸው ላይ

x