am_tn/isa/14/18.md

2.5 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገሮች

ይህ እስራኤላውያን የባቢሎን ንጉሥ ላይ ሲያዜሙ ከነበረው የፌዝ ዜማ የመጨረሻ ክፍል ነው፡፡

ሁሉም በክብር ተጋድመዋል

ይህ ማለት ሥጋቸው በክብር ተቀብሯል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክብር ባለው ሁኔታ የተቀበሩ ነገሥታት ሁሉ››

ነገር ግን ከመቃብር ወጥተህ ተጥለሃል

ከመቃብር ወጥቶ መጣል መጀመሪያውኑ አለመቀበርን ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ግን አልተቀበርህም፤ ሥጋህ መሬት ላይ ቀርቷል››

እንደሚጣል ቅርንጫፍ

የተጣለ ቅርንጫፍ ዋጋ የሌለው ነገርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወዲያ እንደሚጣል የማይረባ ቅርንጫፍ››

ሙታን እንደ መጐናጸፊያ ይሸፍኑሃል

ይህ ማለት ብዙ ሙታን እርሱ ላይ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሙታን አካል ጨርሶ ይሸፍንሃል›› ወይም፣ ‹‹የሞቱ ወታደሮች ሬሳ ይከመርብሃል››

በሰይፍ የተወጉት

ይህ የሚገልጸው በዚህ ዐረፍተ ነገር መጀመሪያ ላይ ተነሥተው የነበሩትን፣ ‹‹ሙታን›› ነው፡፡ በሰይፍ መወጋት በጦርነት መገደል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጦርነት የተገደሉ››

ወደ ጥልቁ ድንጋዮች በወረዱት

ጥልቁ የሚለው የሚያመለክተው ገሃነምን ወይም ብዙ የሞቱ ሰዎች የሚጣሉበት ምድር ላይ ያለ ሰፊ ጉድጓድን ነው፡፡

ከእነርሱ ጋር በመቃብር አትሆንም

‹‹እነርሱ›› የተባሉት ሞተው በሚገባ የተቀበሩት ሌሎች ነገሥታት ናቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር በመቃብር መሆን እነርሱ እንደ ተቀበሩ መቀበር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌሎች ነገሥታት እንደ ተቀበሩ አትቀበርም››

የክፉ አድራጊዎች ዘር ጨርሶ አይታወስም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ስለ ክፉ አድራጊዎች ዘር የሚናገር አይኖርም››