am_tn/isa/14/15.md

1.4 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገሮች

ይህ እስራኤላውን የባቢሎን ንጉሥ ላይ የሚያዜሙት የፌዝ ዜማ ክፍል ነው፡፡

አሁን ወደ ሲኦል ወርደሃል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁን ግን እግዚአብሔር ወደ ሲኦል ጥሎሃል››

ሰውየው ይኽ ነው?

ሰዎች እንዲህ በማለት የሚጠይቁት በባቢሎን ንጉሥ ላይ ለማፌዝ ወይም በእርሱ ላይ በደረሰው የተሰማቸውን ድንጋጤ ለመግለጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መቼም ሰውየው ይኼ ሊሆን አይችልም››

ምድርን ያናወጠ

ይህም ማለት 1) የንጉሡ ሰራዊት ሕዝብን ድል ለማድረግ ሲገሠግሥ ምድር ተናወጠች ማለት ሊሆን ይችላል፤ ወይም 2) የምድር ሕዝብ እርሱን በመፍራት ተንቀጠቀጡ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

መንግሥታትን ያንቀጠቀጠ

ይህም ማለት 1) መንግሥታትን ድል ማድረግን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል ወይም 2) ‹‹መንግሥታትን ማሸበርን›› የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡

ዓለምን ምድረ በዳ ያደረገ

‹‹ሰዎች የሚኖሩባቸውን ቦታዎች ምድረ በዳ ያደረገ››