am_tn/isa/14/12.md

1.8 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ይህ እስራኤላውያን የባቢሎን ንጉሥ ላይ የሚያዜሙት የፌዝ ዜማ ክፍል ነው፡፡

አንተ የንጋት ልጅ የአጥቢያ ኮከብ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ

የንጋት ኮከብ ከመንጋቱ በፊት የሚወጣ ደማቅ ኮከብ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ታላቅ እንደ ነበር፣ አሁን ግን ምንም ማለት እንዳልሆነ ለማመልከት የእስራኤል ሕዝብ ስለ ባቢሎን ንጉሥ ይናገራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ንጋት ኮከብ ደማቅ ነበርህ፤ አሁን ግን ከሰማይ ወድቀሃል››

እንዴት ተቆርጠህ ወደ ምድር ተጣልህ

የእስራኤል ሕዝብ የባቢሎን ንጉሥ ተቆርጦ የተጣለ ዛፍ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተቆርጦ ወደ መሬት እንደ ተጣለ ዛፍ ተሸንፈሃል››

በመሰብሰቢያ ተራራ እቀመጣለሁ

ይህ የሚያመለክተው በቅርብ ምሥራቅ የነበሩ አብዛኞቹ ሰዎች የከነዓናውያን አማልክት ከሶርያ በስተ ሰሜን ባለው ቦታ ተራራ ጫፍ ላይ እንደሚሰበሰቡ እንደሚያውቀ ነው፡፡ ተራራ ላይ መቀመጥ ከአማልከት ጋር መግዛትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አማልክት በሚሰበሰቡበት ተራራ ላይ እገዛለሁ››

በሰሜን በኩል ጫፍ ላይ

‹‹በሰሜን በኩል ርቆ›› በሰሜን ያለው ተራራ ዛፎን ተብሎ ነበር የሚጠራው፡፡ አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች፣ ‹‹በዛፎን በኩል ሩቅ ቦታ›› ይላሉ፡፡