am_tn/isa/14/07.md

2.1 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ይህ እስራኤላውያን የባቢሎን ንጉሥ ላይ የሚያዜሙት የፌዝ ዜማ ክፍል ነው፡፡

ምድር ሁሉ

ይህ በምድር የሚኖረውን ሁሉ ይመለከታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር የሚኖር ማንኛውም››

ጥድና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ በአንተ ላይ ደስ አላቸው

ኢሳይያስ ዛፎች ደስ እንደሚላቸው ሰዎች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ይህም እግዚአብሔር የባቢሎንን ንጉሥ ማስቆሙ ታላቅ ነገር ስለሆነ፣ ቢችል ኖሮ ሌላው ቀርቶ ተፈጥሮ እንኳ ደስ እንደሚለው አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጥድ ዛፍና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ ሳይቀር፣ በአንተ ላይ በደረሰው ደስ ይላቸዋል››

በአንተ ላይ ደስ ይላቸዋል

ደስ የሚላቸው ለምን እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ዐቅም ስላሳጣህ ደስ ይላቸዋል››

ዝቅ ዝቅ ብለሃልና

ዝቅ ዝቅ ማለት ዐቅመ ቢስና ዋጋ የሌለው መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐቅመ ቢስ ሆነሃልና››

ከበታችህ ሲኦል ልትቀበልህ ጓጉታለች

ሲኦል እንግዶችን የሚቀበል ሰው ተደርጐ ተነግሯል፡፡ ይህ የሚመለክተው ንጉሡ እንደሚሞት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሲኦል አንተን ለማስተናገድ ዝግጁ ናት››

እንዲቀበሉህ ሙታንን፣ የምድር ነገሥታትን ሁሉ ያስነሣል

‹‹ሙታንን፣ የምድር ነገሥታትን ሁሉ ያነቃል፡፡›› ሲኦል ውስጡ ላሉት የሚነቃ ሰው ተደርጐ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሲኦል ውስጥ ያሉ የሞቱ የምድር ነገሥታት ሁሉ እንኳን መጣህ ሊሉህ ይነቃሉ››