am_tn/isa/14/05.md

1.4 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ይህ እስራኤላውያን የባቢሎን ንጉሥ ላይ የሚያዜሙት የፌዝ ዜማ ክፍል ነው፡፡

ያህዌ የክፉዎችን ዘንግ ሰብሮአል

የክፉዎች ዘንግ ክፉዎች ሌሎች ሰዎችን የሚመቱበትን ዘንግ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ ዘንጋቸውን መስበር ሌሎች ላይ የሚያደርሱትን ጭካኔ ኀይል መስበር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የክፉዎችን ኀይል ደምስሶአል፡፡››

የገዦች በትረ መንግሥት

በትረ መንግሥት የሚያመለክተው የመግዛትን ሥልጣን ነው፡፡ በትረ መንግሥቱን መስበር የገዢውን ሥልጣን መደምሰስ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የክፉ ገዦችን ሥልጣን ደምስሶአል፡፡››

ሕዝቦችን የመታውን

‹‹ሕዝቦችን ሲመታ የነበረውን›› ክፉዎች በበትራቸው ሰዎችን ይመታሉ፡፡

በማያቋርጥ ምት

‹‹ማቆሚያ የሌለው›› ወይም፣ ‹‹ደግሞ ደጋግሞ››

ሕዝቦችን ያስገበረውን

‹‹ሌሎች አገሮችን ድል ያደረገውን››

ያለ መከልከል የመታውን

‹‹ማቆሚያ የሌለው ጥቃት››