am_tn/isa/14/03.md

1.0 KiB

ከሥቃይህና ከመከራህ

‹‹የአንተ›› የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ቢሆንም፣ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ እንዲሁም፣ ‹‹ሥቃይ›› እና፣ ‹‹መከራ›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ቢሆኑም፣ በአንድነት ጥቅም ላይ የዋሉት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም እንድትሠቃይ ካደረጉህ ነገሮች››

ጨቋኙ እንዴት አበቃለት

‹‹ጨቋኙ አበቃለት›› ይህ ቃለ አጋኖ ነው፡፡

የትዕቢተኛም ቁጣ አበቃለት

‹‹የትዕቢተኛ ቁጣ›› የሚለው የሚያመለክተው ሌሎች ሕዝቦችን በጭካኔ ያሠቃይ የነበረውን የባቢሎንን ንጉሥ ትዕቢት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጭካኔው አበቃለት›› ወይም፣ ‹‹ከእንግዲህ ሕዝብን አይጨቁንም››