am_tn/isa/12/03.md

1.4 KiB

ከድነት ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ

የዳኑት ሰዎች ከምንጭ ውሃ እንዳገኙ ሰዎች እንደሆኑ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ከምንጭ ውሃ ሲቀዱ ደስ እንደሚላቸው እርሱ ሲያድናችሁ እናንተም ደስ ይላችኃል››

ስሙንም ጥሩ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ስሙ›› የተባለው ያህዌ ነው፡፡ ስሙን ጥሩት ማለት እርሱን ማመስገንን ወይም የእርሱን ርዳታ መለመንን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ አመስግኑት›› ወይም፣ ‹‹እንዲረዳችሁ ጥሩት››

ያደረገውን በአሕዛብ መካከል አስታወቁ

‹‹ያደረገውን›› የሚለውን፣ ‹‹እርሱ አድርጐ የነበረውን›› በሚል ሐረግ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ያደረገውን ታላላቅ ነገሮች ለሕዝብ ተናገሩ››

ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን ዐውጁ

‹‹ስሙ›› የሚያመለክተው፣ ያህዌን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ከፍ ከፍ ያለ መሆኑን ዐውጁ›› ወይም፣ ‹‹እርሱ ታላቅ መሆኑን ዐውጁ››