am_tn/isa/11/14.md

1.1 KiB

በፍልስጥኤም ተራሮች ላይ ቁልቁል ይበርራሉ

የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሰውን ወይም እንስሳን ለማጥቃት በድንገት ቁልቁል በሚበሩ ወፎች ተመስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እዚያ ያሉትን ሰዎች ለማጥቃት ወደ ፍልስጥኤም ተራሮች በፍጥነት ይሄዳሉ››

የግብፅ ባሕረ ሰላጤ

‹‹ባሕረ ሰላጤ›› በከፊል በመሬት የተከበበ ትልቅ የውሃ አካል ነው፡፡

በሚጋረፍ ነፋስ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ያንቀሳቅሳል

እጁን በአንዳች ነገር ላይ ማንቀሳቀሱ የመለወጥ ኀይሉን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በታላቅ ኀይሉ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ የሚጋረፍ ነፋስ ያነፍሳል››

የሚጋረፍ ነፋስ

ይህ ጥቂቱን የወንዞች ውሃ የሚያደርቅ ሞቃት ነፋስ ነው፡፡

ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ

‹‹ሰዎች ጫማቸውን እንዳደረጉ እንዲሻገሩት››