am_tn/isa/11/08.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ንጉሡ በሚገዛበት ጊዜ በዓለም የሚኖረውን የተሟላ ሰላም መግለጹን ቀጥሏል

ሕፃን ልጅ በእባብ ጉድጓድ ይጫወታል

እባቡ ስለማይነድፈው ልጁ ደህና እንደሚሆን በግልጽ መነገር አለበት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕፃናት ምንም ሳይጐዳቸው በእባብ ጉድጓድ ላይ ይጫወታሉ››

እባብ… የእባብ ጉድጓድ

ይህ የሚያመለክተው በጠቅላላ መርዛማ እባቦችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እባቦች… የእባቦች ጉድጓድ››

ጡት የጣለ ሕፃን

የእናቱን ጡት ወተት መጠጣት ያቆመ

በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ

‹‹የተቀደሰ ተራራ›› በኢየሩሳሌም ያለው የጽዮን ተራራ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ቅዱስ ተራራ ሁሉ››

ምድር ያህዌን በማወቅ ትሞላለች

‹‹ያህዌን በማወቅ›› የሚለው ሐረግ ያህዌን የሚያውቁ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምድር ያህዌን በሚያውቁ ሰዎች ትሞላለች›› ወይም፣ ‹‹ያህዌን የሚያውቁ ምድርን ይሸፍናሉ››

ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን

ይህ ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው ምድር ምን ያህል ያህዌን በሚያውቁ ሰዎች እንደምትሞላ ለማሳየት ነው፡፡ ቃሎቹ ከቀደመው ሐረግ ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ ይህ እንደሚሆን የበለጠ ግልጽ ይሆናል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ውሃ ባሕሮችን እንደሚሞላ››