am_tn/isa/11/03.md

3.4 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ኢሳይያስ ስለ ንጉሡ መናገሩን ቀጥሏል

ዐይኑ እንዳዬ አይፈርድም

‹‹ዐይኑ እንዳዬ›› የሚለው ሐረግ ሰውየው ላይ ለመፍረድ የሚያስችሉ አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችን ማየትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ውጫዊ ሁኔታውን በማየት ብቻ ሰውየው ላይ አይፈርድም››

ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም

‹‹ጆሮው በሚሰማው አይወስንም›› - ‹‹ጆሮው እንደ ሰማ›› የሚለው ሐረግ ሰዎች ስለ ሌላው ሰው የሚናገሩን መስማት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌሎች ስለ እርሱ የሚናገሩትን በመስማት ብቻ ማንም ላይ አይፈርድም››

ለድኾች… ለምስኪኖች… ለክፉዎች

እነዚህ ቃሎች እነዚህ ባሕርያት ያሏቸውን ሰዎች ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድኾች ሰዎች… ምስኪን ሰዎች… ክፉዎች ሰዎች››

በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል

ሁለቱም ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው

በአፉ በትር ምድርን ይመታል

‹‹ምድር›› በምድር የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ በአፉ እስትንፋስ መምታት እነርሱ ላ መፍረድንና ፍርዱም ወደ ቅጣት ማድረሱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር ሕዝብ ላይ ይፈርዳል፤ እነርሱም ይቀጣሉ››

በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል

‹‹የከንፈሩ እስትንፋስ›› እነርሱ ላይ መፍረድን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ክፉዎች ላይ ይፈርዳል፤ እነርሱም ይገደላሉ››

የወገቡ መታጠቂያ… የጐኑ መቀነት

ይህም ማለት፣ 1) መታጠቂያ መሥራት እንዲችል የሰውን ልብስ ለመያዝ ይጠቅማል፡፡ ወይም 2) መታጠቂያ በውስጥ የሚለበስ ነው ወይም 3) መታጠቂያ ሥልጣኑን ለማሳየት ንጉሡ የሚለብሰው መጐናጸፊያ ነው፡፡

ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ ይሆናል

እንደ ቀበቶ ጽድቅን ወገብ ላይ መታጠቅ ጻድቅ መሆንን ይወክላል፡፡ ይህም ማለት፣ 1) የንጉሡ ጽድቅ ለመግዛት ያስችለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጽድቅ ይገዛል››

ታማኝነትም የጐኑ መቀነት

እዚህ ሐረግ ላይ፣ ‹‹ይሆናል›› የሚለው ውስጠ ታዋቂ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታማኝነት ጐኑ ላይ መቀነት ይሆናል››

ታማኝነት የጐኑ መቀነት

እንደ መቀነት ታማኝነትን መታጠቅ ታማኝ መሆንን ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት፣ 1) የንጉሡ ታማኝነት ለመግዛት ያስችለዋል ማለት ነው፣ ወይም 2) የንጉሡ ታማኝነት ለመግዛት ያለውን ሥልጣን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታማኝነት እንደ መቀነት ጐኑ ላይ ይሆናል›› ወይም፣ ‹‹በታማኝነት ይገዛል››