am_tn/isa/10/26.md

3.0 KiB

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

በጅራፍ ይገርፋቸዋል

‹‹አሦራውያንን በአለንጋ ይገርፋቸዋል›› እግዚአብሔር በእርግጥ ጅራፍ አይጠቀምም፡፡ ይህ የሚያመላክተው አሦራውያንን በጽኑ ለመቅጣት እግዚአብሔር ያለውን ኀይል ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጅራፍ እንደሚገረፍ አሦራውያንን በጣም ይቀጣል››

በሔሬብ ዐለት አካባቢ ምድያምን እንደ መታ

ይህ የሚያመለክተው የምድያምን ጦር ድል እንዲያደርግ ጌዴዎን የሚባለውን ሰው እግዚአብሔር መርዳቱን ነው፡፡

በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በትሩን በባሕር ላይ ያነሣል

ይህ የሚያመለክተው እነርሱ የግብፃውያን ሠራዊት የነበሩ ይመስል፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከአሦራውያን ማዳኑን ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው እስራኤላውያን ከግብፃውያን ሰራዊት እንዲያመልጡና የግብፃውያን ሰራዊት ግን ሰጥሞ እንዲቀር እግዚአብሔር ቀይ ባሕር እንዲከፈል ማድረጉን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አባቶቻችሁ ከግብፅ ሰራዊት እንዲያመልጡ እንደ ረዳቸው ሁሉ እናንተም ከአሦር ሰራዊት እንድታመልጡ ይረዳችኃል፡፡››

ሸክሙ ከትከሻህ ቀንበሩም ከዐንገትህ ላይ ይነሣል

‹‹አሦር ትከሻህ ላይ ያደረገውን ሸክም ያህዌ ያነሣል፤ ዐንገትህ ላይ ያስቀመጡትንም ቀንበር ያህዌ ያስወግዳል ሁለቱ ሐረጐች የሚሉት በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ‹‹ሸክም›› እና፣፣ ‹‹ቀንበር›› የሚያመለክቱት ባርነትን ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የጨቆኑህን አሦራውያን ያስወግዳል፤ አንተን ባርያቸው እንዳያደርጉም ያስቆማቸዋል››

ቀንበሩ ከውፍረት የተነሣ ይሰበራል

አገላለጹ ቀንበሩን የሚሸከመው እንስሳ ዐንገት በጣም እንደሚወፍርና ከዚያ በኃላ ለቀንበሩ ተስማሚ እንደማይሆን ያመለክታል፡፡ ይህ የሚያመለክተው እስራኤል በጣም ብርቱ እንደሚሆንና ከእንግዲህ አሦራውያን እርሱን መግዛት የማይችሉ መሆናቸውን ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐንገትህ በጣም ከመወፈሩ የተነሣ ቀንበር ይሰበራል›› ወይም፣ ‹‹በጣም ብርቱ ስለምትሆን ከእንግዲህ የአሦራውያን ባርያ አትሆንም››