am_tn/isa/10/24.md

1.5 KiB

አሦራውያን

ኢሳይያስ እንደ አንድ ሰው አድርጐ ስለ አሦር ንጉሥና ስለ ሰራዊቱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአሦር ንጉሥና ሰራዊቱ››

በበትር ይመታሃል፤ ሽመል ያነሣብሃል

‹‹በትር›› እና፣ ‹‹ሽመል›› የተሰኙት ቃሎች ሰዎች እንስሳትን ወይም ሌሎች ሰዎችን ለመምታት የሚጠቀሙባቸው እንጨቶች ናቸው፡፡ አሦራውያን እስራኤላውያንን ስለሚገዙበት መንገድ ነው ኢሳይያስ እየተናገረ ያለው፤ አሦራውያን እስራኤላውያንን በበትር ይመቷቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንተን ይገዛል፤ ባርያዎቹም ያደርጋችኃል››

ይመታል

‹‹እርሱ›› የሚለው የአሦር ንጉሥና ሰራዊቱን የሚወክለው ‹‹አሦርን›› ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱና ሰራዊቱ ይመታሉ››

ግብፃውያን እንዳደረጉት

ይህ ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ግብፃውያን አባቶችህን እንደ ገዙና ባርያዎች እንዳደረጓቸው››

በቁጣዬ ይጠፋል

ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእርሱ ላይ ስለ ተቆጣሁ አጠፋዋለሁ››