am_tn/isa/10/22.md

2.1 KiB

እስራኤል ሕዝብህ

እዚህ ላይ ‹‹የአንተ›› ነጠላ ቁጥር ነው፡፡ ይህም ማለት፣ 1) እግዚአብሔር ለኢሳይያስ እየተናገረ ነው፤ ‹‹አንተ›› የሚለው ኢሳይያስን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአንተ ሕዝብ እስራኤል›› ወይም 2) ለእስራኤል ሕዝብ ኢሳይያስ ወይም እግዚአብሔር እየተናገሩ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ‹‹የአንተ›› የእስራኤልን መንግሥት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እስራኤል ሆይ፣ ሕዝብህ››

በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ናቸው

ይህ አጽንዖት የሚሰጠው የእስራኤል ሕዝብ ቁጥር በጣም ብዙ እንደሚሆን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ መቆጠር አይችሉም››

ጥፋት ታውጆአል

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእስራኤል የሚኖሩ ብዙዎችን ለማጥፋት ያህዌ ወስኖአል››

እንደ ወንዝ እየፈሰሰ ያለው ጽድቅ፣ ይህ እንዲሆን ግድ ይላል፡፡

ይህን እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ መሆን ያለበት ፍጹም ከሆነው ጽድቅ የተነሣ ነው›› ወይም፣ ‹‹እርሱ ፍጹም ጻድቅ ስለሆነ ያህዌ ይህን ማድረግ ይኖርበታል፡፡››

የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል

ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ ይህም ማለት፣ 1) አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ እንደ ወሰነው በምድሪቱ ያለውን ማንኛውንም ነገር ያጠፋል›› ወይም 2) አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ እንደ ወሰነው በምድሪቱ ያለውን ሕዝብ ያጠፋል››

እንደ ወሰነ

‹‹እንዳቀደው››