am_tn/isa/10/17.md

1.3 KiB

የእስራኤል ብርሃን እሳት ይሆናል

‹‹የእስራኤል ብርሃን›› የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ እየተናገረ ያለው ያህዌ ወይም ኢሳይያስ መሆኑ ግልጽ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል ብርሃን አኔ ያህዌ፣ የማያከብረኝን ሁሉ ማጥፋት እንደሚችል እሳት እሆናለሁ››

ቅዱሱም ነበልባል ይሆናል

‹‹የእስራኤል ቅዱስ እኔ ያህዌ እንደ ነበልባል እሆናለሁ›› ኢሳይያስ 1፥4 ላይ፣ ‹‹ቅዱስ›› የሚለውን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

እሾኹንና ኩርንችቱን ሁሉ እሳት ይበላዋል

‹‹እሳቱ የአሦር ንጉሥ እሾኽና ኩርንችት ይበላዋል›› ተናጋሪው የአሦርን ንጉሥ ሰራዊት ከእሾኽና ከኩርንችት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ምን ያህል በቀላሉ እንደሚያጠፋው አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እሾኹንና ኩርንችቱን እንደሚበላ እሳት አሦራውያንን አጠፋለሁ››