am_tn/isa/10/15.md

2.2 KiB

መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን፤ መጋዝስ ከሚጠቀምበት ሰው ይበልጥ ራሱን ያመሰግናልን?

ተናጋሪው እነዚህን ጥያቄዎች የሚያቀርበው በአሦር ንጉሥ ለመሳለቅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መጥረቢያ ከሚጠቀምበት ሰው የበለጠ እንደሆነ አይኩራም፤ መጋዝም ከሚቆርጥበት ሰው የበለጠ ክብር አያገኝም››

መጋዝ

እንጨት ለመቁረጥ የሚያገለግል ስለታም መሣሪያ

በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ ወይም የእንጨት ዱላ ሰውን እንደሚያነሣ አድርጐ እንደሚኩራራ ነው

እነዚህ ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፤ ጥቅም ላይ የዋሉት የሁለቱን ጥያቄዎች ትርጒም ለማጠናከር ነው፡፡ ይህን በአዲስ ዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በትርም ሆነ ዱላ በሚያነሣው ሰው ላይ አይኩራራም››

ስለዚህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ በምርጥ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል

እየተናገረ ያለው ያህዌ ወይም ኢሳይያስ መሆኑ ግልጽ አይደለም፡፡ ‹‹የሚያከሳ›› የሚለውን፣ ‹‹የሚያደክም›› በማለት መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ፣ ብርቱዎቹን የንጉሡን ወታደሮች ያደክማል››

ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኮሳል

ያህዌ የእርሱን ቅጣት ከእሳት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው የእርሱ ቅጣት የአሦርን መንግሥት ውበትና ታላቅነት ሁሉ ጨርሶ የሚያወድም መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ የታበየበትን ማንኛውንም ነገር የሚያጠፋ እሳት በመሆን ታላቅነቱን ሁሉ አወድማለሁ››