am_tn/isa/10/14.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

አሁንም ያህዌ የአሦር ንጉሥ የተናገረውን እየተናገረ ነው፡፡ (ኢሳይያስ 10፥13 ይመ.)

በእጄ ያዝሁ

እጅ የንጉሡን ወይም የሰራዊቱን ኀይል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኅይሌ ያዝሁ›› ወይም ‹‹ሰራዊቴ ያዘ››

ከወፍ ጐጆ እንደሚይዝ የሕዝቦችን ሀብት ያዝሁ

የአሦር ንጉሥ የሕዝቦችን ሀብት መውሰዱን ወፍ ጐጆ ውስጥ ያለውን ዕንቁላል ከሚወስድ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህም እነዚያን ሕዝቦች ድል ማድረግ ለእርሱና ለሰራዊቱ ምን ያህል ቀላል እንደ ነበር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዕንቁላል ከወፍ ጐጆ እንደሚሰበሰብ፣ ሰራዊቴ የሕዝቦችን ሀብት በቀላሉ ዘረፈ››

የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበሰብ እኔም ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ

የአሦር ንጉሥ መንግሥታትን መውሰዱን ዕንቁላል ከመውሰድ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱን ለመከላከል ወፏ በሌለችበት ጊዜ ከጐጆዋ ዕንቁላሎች እንደሚሰበስብ ሰው፣ ሰራዊቴም ከአገር ሁሉ ሀብት ሰበሰበ››

ክንፉን ያራገበ አልነበረም፤ አፉን ከፍቶ የጮኸ አልነበረም

ይህ ሕዝቦችን ዕንቁላሎቿ ሲወሰዱ ዝም ብላ ከምታይ ወፍ ጋር ያመሳስላቸዋል፡፡ ይህም የአሦር ንጉሥ ሰራዊት ሀብታቸውን ሁሉ ሲወስድ ሕዝቦች ምንም አለማድረጋቸውን አጽንዖት ይሰጣል›› አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዕንቁላሎቿ ሲሰረቁ ድምፅ እንደማታሰማ ወይም ክንፏን እንደማታራግፍ ወፍ፣ እኛ ሀብታቸውን ስንዘርፍ ሕዝቦች ምንም አላደረጉም››