am_tn/isa/10/12.md

2.0 KiB

ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ከፈጸመ በኃላ እቀጣዋለሁ፡፡

ያህዌ ስለ ራሱ እንደሌላ ሰው ይናገራል፡፡ ‹‹እኔ ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የምሠራውን ከፈጸምሁ በኃላ እቀጣዋለሁ››

የሚያደርገው… ላይ

የመቅጣቱ ሥራ፡፡ ‹‹እቀጣለሁ… እቀጣዋለሁ››

የአሦርን ንጉሥ ልብ እብሪትና የንቀት አመለካከት እቀጣለሁ

‹‹ስለ ተናገረው እብሪትና የትዕቢት አመለካከቱ የአሦርን ንጉሥ እቀጣለሁ››

እንዲህ ብሏልና

‹‹የአሦር ንጉሥ እንዲህ ብሏልና››

አፈረስሁ… ዘረፍሁ

‹‹እኔ›› የሚለው የሚያመለክተው የአሦርን ንጉሥ ነው፡፡ እርሱ የአሦር ሰራዊት መሪ ስለ ነበር በእርሱ ትእዛዝ ሰራዊቱ ስላደረገው ሁሉ ክብሩን ይወስድ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰራዊቴ አፈረሰ… ዘረፈ››

እንደ ወይፈን

‹‹እንደ ወይፈን የበረታ›› አንዳንድ የጥንት ቅጂዎች፣ ‹‹እንደ ኀያል ሰው›› ይላሉ፡፡

ነዋሪዎቹን አዋረድሁ

ይህም ማለት፣ 1) የአሦር ንጉሥ ድል ያደረጋቸው አገሮችን ሕዝቦች አዋርዶ ነበር፤ ወይም 2) ከእንግዲህ መግዛት እንዳይችሉ የአሕዛብ ነገሥታትን አስወግዶ ነበር ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ሰበሰብሁ

‹‹እኔ›› የሚያመለክተው የአሦርን ንጉሥ ነው፡፡ የአሦር ሰራዊት መሪ ስለ ነበር በእርሱ ትእዛዝ ሰራዊቱ ላደረገው ሁሉ ክብር ይወስድ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔና ሰራዊቴ ሰበሰብን›› ወይም፣ ‹‹እኛ ሰበሰብን››