am_tn/isa/10/10.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ የአሦር ንጉሥ የተናገረውን መናገር ቀጥሏል፡፡

እጄ፣ እንዳሸነፈች ሁሉ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› ወታደራዊ ብርታትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብርቱ የሆነው ሰራዊት ድል እንዳደረገ ሁሉ›› ወይም፣ ‹‹እኔ ድል እንዳደረግሁ››

የእኔ

ይህ የሚያመለክተው የአሦርን ንጉሥ ነው፡፡

ምስሎቻቸው የበለጡትን

በዚያ ዘመን የጣዖቱ ትልቅነት ያንን የሠራውን መንግሥት ትልቅነት ያመለክታል በማለት ሰዎች ያምኑ ነበር፡፡ የአሦር ንጉሥ የኢየሩሳሌም ጣዖቶች ድል ያደረጋቸው አገሮች ጣዖቶችን ያህል ትልልቅ አልነበሩም፤ ስለዚህም እርሱን ለመቋቋም ኢየሩሳሌም ያላት ጉልበት በጣም ታናሽ እንደሆነ መናገሩ ነበር፡፡

በሰማርያና ከንቱ በሆኑት ጣዖቶቿ እንዳደረግሁ

‹‹ሰማርያ›› የሚለው ቃል እዚያ የነበሩ ሰዎችን፣ ‹‹የእርሷ›› የሚለው የሰማርያ ከተማን ያመለክታል፡፡ ከተሞችና አገሮች ብዙውን ጊዜ በእንስታዊ ጾታ ይጠሩ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰማርያ ሕዝብና ከንቱ በሆኑ ጣዖቶቿ እንዳደረግሁ››

በኢየሩሌምና በጣዖቶቿስ እንዲሁ አላደርግምን?

የአሦር ንጉሥ ይህን ጥያቄ ያቀረበው የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ድል እንደሚያደርግ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኢየሩሳሌምና በጣዖቶቿም በእርግጥ ይህንኑ አደርጋለሁ››