am_tn/isa/10/07.md

1.9 KiB

እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም

‹‹እንዲህ›› እና፣ ‹‹ይህ›› የተሰኙትን ቃሎች የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአሦር ንጉሥ እኔ የነገርሁትን ለማድረግ አላሰበም፤ እንደ መሣሪያ እየተጠቀምሁበት እንደ ነበረም አላስተዋለም ነበር››

ዕቅዱ ለማጥፋት፣ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር

‹‹ማጥፋት›› እና፣ ‹‹መደምሰስ›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ጥቅም ላይ የዋሉት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙ ሕዝቦችን ፈጽሞ ለመደምሰስ ይፈልጋል››

የጦር አዛዦቼ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?

የአሦር ንጉሥ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ሁሉም ማወቅ አለበት ብሎ ለሚያስበው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድል ባደረግሁት አገር ሁሉ ላይ ነገሥታቴን የጦር አዛዦች አድርጌአለሁ››

ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማት እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?

የአሦር ንጉሥ እነዚህን ጥያቄዎች ያቀረበው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ካልኖ ከኩርኩማሽ የተለየች አይደለችም፤ ሐማት ከአርፋድ የተለየች አይደለችም፤ ሰማርያም ከደማስቆ የተለየች አይደለችም፤ እኔ ሁሉንም ድል አድርጌአለሁ››

ካልኖ… ከርከሚሽ… ሐማት… አርፋድ

እነዚህ ሁሉ የከተሞች ስም ናቸው፡፡