am_tn/isa/10/05.md

3.0 KiB

ወዮ

ይህ ቃል አሦር ላይ እግዚአብሔር የሚያመጣው ቅጣት መጀመሩን ያመለክታል፡፡

አሦራውያን

ይህ የሚያመለክተው የአሦርን ነገሥታት ነው፡፡

የቁጣዬ በትር የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው

ሁለቱም በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ያህዌ የአሦር ንጉሥን እጁ ላይ መሣሪያ ከያዘና በዚያም ሌሎችን ከሚመታ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህም የአሦር ንጉሥና ሰራዊቱ ያህዌ እስራኤልን የሚቀጣበት መሣሪያዎች መሆናቸውን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቁጣዬን ለማሳየት የምጠቀምበት እጄ ላይ እንዳለ መሣሪያ ለሆነ››

እልከዋለሁ… አዝዘዋለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እርሱ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአሦርን ንጉሥ ነው፡፡ እግዚአብሔር ንጉሡን ብቻ ሳይሆን፣ ከእርሱ ጋር የአሦርን ሰራዊም የላከ ይመስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአሦርን ሰራዊት እልካለሁ… አዝዛቸዋለሁ››

እብሪተኛ ሕዝብ ላይ፣ የሚፈስሰው ቁጣየን የሚሸከም ሕዝብ ላይ

‹‹ትዕቢት የሚላበትን እኔንም በጣም ያስቆጣኝን ሕዝብ እንዲቀጣ››

የሚፈስሰውን ቁጣዬን የሚሸከም

የእርሱ ቁጣ መያዣው ከሚችለው በላይ ሞልቶ እንደሚፈስስ ነገር እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፣ ‹‹ሕዝቡ›› ይህን መያዣ ለመሸከም ቢሞክሩም በጣም ከባድ ነበር፤ ሞልቶ መፍሰስ ከጀመረ በኃላ እንኳ ይህዌ መጨመሩን ቀጥሏል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከቀጣኃቸው በኃላ እንኳ አሁንም የተቆጣሁት ሕዝብ››

ምርኮ እንዲያግበሰብስ

‹‹ያላቸውን ሁሉ እንዲወስድ››

የሚታደነውን እንዲወስድ

እንደ ታዳኝ ነገር ሕዝቡን እንዲወስድ፡፡ ‹‹ታዳኝ›› የሚለውን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ኢሳይያስ 5፥29 ተመልከት፡፡

እንደ ጭቃ እንዲረግጣቸው

ይህ ማለት፣ 1) የአሦር ሰራዊት እስራኤልን ማጥቃቱን ጭቃው ምን እንደሚሆን ደንታ ሳይኖረው ጭቃው ላይ ከሚረማመድ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ጭቃ እስኪሆኑ ድረስ ይረግጣቸዋል›› ወይም 2) እንደ ጭቃ እስኪሆኑና መነሣት እስከማይችሉ ድረስ ሕዝቡ ሌሎች ሰዎችን ይረግጣሉ፡፡ ይህ የሚያመለክተው ሙሉ በሙሉ እንደሚያሸንፏቸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ፈጽሞ ያሸንፏቸዋል››