am_tn/isa/10/03.md

2.1 KiB
Raw Permalink Blame History

በፍርድ ቀን ምን ታደርጋላችሁ… ምን ይውጣችኃል?

ኢሳይያስ ጥያቄውን ያቀረበው ድኻውንና ደካማውን የሚጐዱ በይሁዳ ያሉ ሰዎችን ለመገሠጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍርድ ቀን ምንም ማድረግ አትችሉም… ምን ይሻላችኃል!

የፍርድ ቀን

‹‹ያህዌ ለፍርድ ሲመጣ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ እናንተን በሚቀጣበት ቀን››

ርዳታ ለማግኘት ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታደርጉታላችሁ?

ኢሳይያስ ጥያቄውን ያቀረበው ደኻውንና ደካማውን የሚጐዱ በይሁዳ ያሉ ሰዎችን ለመገሠጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ርዳታ ለማግኘት የምትሄዱበት የለም፤ ሀብታችሁን የምትደብቁባትም ቦታ የላችሁም!

ምን አይተርፋችሁም፣ ትሸማቀቃላችሁ

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ከሀብታችሁ ምንም አይተርፍም፤ ትሸማቀቃላችሁ›› ወይም 2) ‹‹ከመሸማቀቅ ሌላ የምታደርጉት ነገር የለም››

በታሰሩ ወይም በሞቱት መካከል ትሸማቀቃላችሁ

‹‹ጠላቶቻችሁ አሥረው ይወስዳችኃል ወይም ትገደላላችሁ››

በዚህ ሁሉ ቁጣው ገና አልበረደም፤

‹‹ይህ ሁሉ ሆኖ እንኳ፣ አሁንም እንደ ተቆጣ ነው›› ኢሳይያስ 5፥25 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

አሁንም እጁ እንደ ተዘረጋ ነው

ኢሳይያስ ያህዌን ሌላውን ሰው ለመምታት እጁን ከዘረጋ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህ ያህዌ እስራኤልን የመቅጣቱ ምሳሌ ነው፡፡ ኢሳይያስ 5፥25 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁንም እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተዘጋጀ ነው››