am_tn/isa/10/01.md

1.4 KiB

ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ ጭቆና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለሰው ሁሉ መልካም ያልሆኑ ሕጐችንና ሥርዐቶችን ለሚያወጡ››

የድኾችን መብት ይጋፋሉ፤ የተጨቆነውን ሕዝቤን ፍትሕ ያዛባሉ

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሕዝቤ መካከል ላሉ ድኾችና ችግረኞች ፍትሕ አያደርጉም››

ችግረኛ

‹‹ድኻ››

መበለቶችን ይበዘብዛሉ

‹‹ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ማንኛውንም ነገር ይወስዳሉ››

ወላጅ የሌላቸውን ያጠቃሉ

ኢሳይያስ ወላጅ የሌላቸውን አራዊት አድነው ከሚበሏቸው እንስሳት ጋር አመሳስሎአቸዋል፡፡ ይህም ወላጅ የሌላቸው ዐቅመ ቢስ መሆናቸውንና ዳኞች በቀላሉ ሊጐዱዋቸው እንደሚችሉ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚያድነውን እንደሚያጠቃ አውሬ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ያጠቃሉ››

ታዳኝ

ኢሳይያስ 5፥29 ላይ እንዳለው፣ ‹‹ታዳኝ›› ተብሎ ተተርጒሞአል፡፡