am_tn/isa/09/18.md

1.7 KiB

ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ ኩርንችቱንና እሾኹን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል

የሕዝቡ ክፉ ሥራ በአውዳሚ እሳት ተመስሎአል፡፡ እሳቱ ከእንግዲህ ሰዎች በማይኖሩባቸው ቦታዎች የሚበቅሉትን፣ ‹‹ኩርንችትና እሾኽ›› ያቃጥላል፤ ሰዎች የሚኖሩባቸውን ቦታዎች ስላጠፋ፣ ከዚያ በፊት ሰው ያልነበረበትን ‹‹ጥቅጥቅ ያለውን ደን›› ያወድማል፡፡

ኩርንችት… እሾኽ

‹‹ኩርንችትና›› እና፣ ‹‹እሾኽ›› ጥቅም የለሽ እሾኻማ ተክሎችን ያመለክታሉ፤ ይህን በአንድ ቃል መተርጐም ይቻላል፡፡ ኢሳይያስ 7፥23 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እሾኻማ ቁጥቋጦ››

በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቁጣ ምድር ትጋያለች

‹‹የሰራዊት ጌታ ያህዌ›› የሚለውን ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ያለውን እንደ ተረጐምህ ተርጉመው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምድርን እንደሚያጋይ እሳት የእግዚአብሔር ጽኑ ቁጣ የእስራኤልንም ሕዝብ ያነዳል››

ማንም ወንድሙን አያድንም

‹‹አያድንም›› ከጥፋት አያወጣም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም የገዛ ወንድሙ እንዲያመልጥ መርዳት አይችልም››