am_tn/isa/09/16.md

1.7 KiB

ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል

ሕዝቡ እንዲያምፅ የሚያደርጉ መሪዎች በተሳሳተ መንገድ የሚመሩ መሪዎች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእስራኤል መሪዎች ሕዝቡ ለእግዚአብሔር እንዳይታዘዝ አደረጉ››

በእነርሱ የሚመሩ ይዋጣሉ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፤ የዚህ ትርጒም፣ 1) አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነርሱ የሚመሩዋቸው ግራ ይጋባሉ›› ማለት ሊሆን ይችላል፤ ወይም 2) አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚመሩትን ያህዌ ያጠፋል›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

አፍ ሁሉ ከንቱ ነገር ይናገራል

‹‹አፍ›› የሚለው ሰውየውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰው ሁሉ ከንቱ ነገር ይናገራል››

በዚህ ሁሉ ቁጣው ገና አልበረደም፤ ይልቁን እጁ

‹‹ይህ ሁሉ ሆኖ እንኳ፣ አሁንም እንደ ተቆጣ ነው፤ እጁም›› ኢሳይያስ 5፥25 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

እጁ እንደ ተዘረጋ ነው

ኢሳይያስ ያህዌን ሌላውን ሰው ለመምታት እጁን ካነሣ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህ ያህዌ እስራኤልን የመቅጣቱ ምሳሌ ነው፡፡ ኢሳይያስ 5፥25 ላይ ይህን እንዴ እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁንም እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተዘጋጀ ነው››