am_tn/isa/09/11.md

1.9 KiB

ስለዚህ ያህዌ ጠላቱ የሆነውን ረአሶንን ያስነሣል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ረአሶን›› የሚወክለው ራሱንና ሰራዊቱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ ያህዌ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ረአሶንና ሰራዊቱን ያስነሣል››

ረአሶን

የሰው ስም፡፡ ኢሳይያስ 7፥1 ላይ ረአሶንን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት

ባለጋራዎቻቸውን ያነሣሣቸዋል

‹‹ያነሣሣል›› ለጥቃት ያነሣሣል ማለትን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የእስራኤልን ጠላቶች ያነሣሣባቸዋል››

አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋቸዋል፡፡

‹‹ይቦጫጭቋቸዋል›› የሚለው የዱር አራዊት የያዙትን እንስሳ እንዴት የሚበሉበትን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዱር አውሬ ሌሎች እንስሳትን እንደሚበላ፣ የጠላት ሰራዊት የእስራኤልን ሕዝብ ያወድማል››

በዚህ ሁሉ ቁጣው ገና አልበረደም፤ ይልቁን እጁም

‹‹ይህ ሁሉ ቢሆን እንኳ አሁንም እንደ ተቆጣ ነው፤ እጁም›› ኢሳይያስ 5፥25 ላይ ይህን እንዴ እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

እጁ እንደ ተዘረጋ ነው፡፡

ኢሳይያስ ያህዌን ሌላውን ሰው ለመምታት ካሰበ ሰው ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህ ያህዌ እስራኤልን እንደሚቀጣ ምሳሌ ነው፡፡ ኢሳይያስ 5፥25 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁንም እነርሱን ለመቅጣት እንደ ተዘጋጀ ነው››