am_tn/isa/09/08.md

1.4 KiB

ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ይወድቃል

‹‹ቃል መላክ›› መናገር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተናገረ››

ያዕቆብ… እስራኤል… ኤፍሬም… ሰማርያ

እነዚህ ስሞች ሁሉ የሚያመለክቱት የሰሜናዊውን የእስራኤል መንግሥት ሰዎች ነው፡፡

ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ

የሚያውቁት ምንን እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ እንደ ፈረደባቸው ሰዎች ሁሉ፣ ኤፍሬምና በሰማርያ የሚኖሩት እንኳ ያውቃሉ››

ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን

ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የፈረሱት ከተሞቻችንን ተራ ጡብ በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንተካዋለን፤ ተራ የሾላ ዛፍ በነበረበትም ቦታ ዝግባ እንተክላለን››