am_tn/isa/09/06.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ስለሚያድንበት ጊዜ መናገሩን ቀጥሏል (ኢሳይያስ 9፥1-2) እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት ወደ ፊት ቢሆንም ኢሳይያስ አሁን እንደ ተፈጸሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ ይህም በእርግጥ እንደሚፈጸሙ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅ ተወልዶልናል

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ‹‹ለእኛ›› የሚለው ቃል ተናጋሪውንና ሰሚዎቹን ያጠቃልላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታ ሕፃን ልጅ ይሰጠናል››

አለቅነት በጫንቃው ላይ ይሆናል

የአለቅነት ሥልጣኑ የገዢነቱ ሥልጣኑ ምልክት የሆነው ልብስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የገዢነት ሥልጣኑን ጫንቃው ላይ ይለብሳል›› ወይም፣ ‹‹እንደ ንጉሥ የሚገዛበት ሥልጣን ይኖረዋል››

መካር

‹‹ነገሥታትን የሚያማክር››

ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም

‹‹ጊዜ እያለፈ ሲሄድ፣ በጣም ብዛት ባላቸው ሰዎች ላይ ይገዛል፤ እጅግ በበዛ ሰላም ውስጥ ይኖራሉ››

በዳዊት ዙፋን ይገዛል

‹‹በዳዊት ዙፋን›› ላይ መቀመጥ የመግዛት መብትን ያመለክታል፤ የእስራኤል ንጉሥ የሚሆኑት የዳዊት ዘሮች ብቻ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ዳዊት ዘር የመግዛት መብት ይኖረዋል››

መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል፡፡

ይህን በአዲስ ዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መንግሥቱ፤ መንግሥቱን ያጸናል፤ ይጠብቃል፤ መልካምና ትክክል የሆነውን ያደርጋል››፡፡

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡