am_tn/isa/09/04.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ስለሚያድንበት ጊዜ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት ወደ ፊት ቢሆንም፣ (ኢሳይያስ 9፥1-2) ኢሳይያስ አሁን እንደ ተፈጸሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ ይህም በእርግጥ እንደሚፈጸም አጽንዖት ይሰጣል፡፡

ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው የከበዳቸውን ቀንበር ሰብረህላቸዋል

የአሦራውያን ባርያዎች የነበሩ እስራኤላውያን ቀንበር እንደ ተሸከመ በሬ መሆናቸውን ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ ይህ የሚሆነው ወደ ፊት ነው፤ እርሱ ግን አሁን እንደ ተፈጸመ አድርጐ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድያም ቀን እንደሆነው ሰው ቀንበርን ከበሬ ላይ እንደሚያነሣ አንተም የጨቋኞቻቸው ባርያዎች የሆኑበን የእስራኤል ሕዝብ ነጻ ታወጣለህ››

የከበደውን ቀንበር… ትከሻው… የተጨቆነበት

ኢሳይያስ የእስራኤል ሕዝብ አንድ ሰው እንዲሆኑ አድርጐ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የከበዳቸው ቀንበር… ትከሻቸው… የተጨቆኑበትን››

ትከሻው ላይ የነበረው ሞፈር

በሬ ትከሻ ላይ የሚውለው ቀንበር አካል ነው

ሞፈር

ሌላው አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በትር›› በሬዎቹ እንዲሠሩ የሚመቱበትንና ሌሎች ላይ ለመግዛት አንድ ሰው ስላለው ኅይል ምሳሌ የሆነ የእንጨት አካል ማለት ነው፡፡

የጨቋኙ በትር

ጨቋኙ የይሁዳ ሕዝብ ላይ የነበረው ኅይል በርትተው እንዲሠሩ በሬዎቹን ለመምታት እንደሚጠቀምበት እንጨት እንደ ነበር ኢሳይያስ ይናገራል፡፡

በምድያም ቀን እንደሆነው

‹‹ቀን›› የሚለው ቃል ከአንድ ቀን በላይ የወሰዱ ድርጊቶችን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ምድያምን እንዳሸነፍህበት ጊዜ››

የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ ይቃጠላል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ በደም የተለወሰውን የወታደሮቹን ጫማና ልብሳቸውን ታቃጥላለህ፡፡››

ለእሳቱ ማገዶ ይሆናል

ይህን በአዲስ ዐረፍተ ነገር በመተርጐም የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይቃጠላል፡፡ ልብሳቸውንና ጫማቸውን ማገዶ ታደርገዋለህ››