am_tn/isa/09/01.md

2.5 KiB

በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ብርሃን ወጣለት

መንፈሳዊ ጉስቁልና ውስጥ ያሉ ሰዎች በድቅድቅ ጨለማ እየተመላለሱ እንደሆነ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጭንቀት ውስጥ ለነበረች ያህዌ ጨለማን ያስወግዳል››

ድንግዝግዝ

ይህ፣ ‹‹ከፊል ወይም ሙሉ ጨለማ›› ማለት ነው፡፡ ኢሳይያስ 8፥22 ላይ ‹‹ድንግዝግዝ›› የሚለውን በተረጐምህበት መንገድ ተርጉመው፡፡

ተጨንቃ ለነበረች

‹‹ከባድ ስቃይና ሀዘን ውስጥ ለነበረች›› ምናልባትም ይህ የይሁዳን ሕዝብ የሚመለከት ሊሆን ይችላል፡፡

በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ

‹‹ምድር›› በዚያ አካባቢ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባለፈው ጊዜ ጌታ በዛብሎንና በንፍታሌም የሚኖሩትን ዝቅ አደረገ››

በኃለኛው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብ ገሊላ ያከብራል

ይህ የሚናገረው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ስለሚወክለው ገለላ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ፊት ጌታ በሜዲትራንያንና በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ባለው መንገድ ላይ ያለውን የአሕዛብ ገሊላን ያከብራል››

የአሕዛብ ገሊላ

‹‹አሕዛብ›› በገሊላ የሚኖሩ የሌላ አገር ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙ ባዕዳን የሚኖሩበት ገሊላ››

በጨለማ የሚኖር… በሞት ጥላ ምድር ለኖሩት

ኢሳይያስ በጨለማ ወይም በሞት ጥላ ምድር ውስጥ ከመኖራቸው የተነሣ የኅጢአትና የመከራ ሕይወት ስለሚኖሩ ሰዎች ይናገራል፡፡

ታላቅ ብርሃን… ብርሃን ወጣላቸው

እዚህ ላይ ‹‹ብርሃን›› ተስፋና መዳንን ይወክላል፡፡

የሞት ጥላ ምድር

‹‹የሞት ጥላ›› የሚለው ድቅድቅ ጨለማ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር››