am_tn/isa/08/19.md

3.2 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እየተናገረ ነው፡፡

የሚያነበንቡትንና የሚያሸኮሽኩትን ሟርተኞችና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ? ወደ ሕጉና ወደ ምስክር ቃሉ ሂዱ

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹መናፍስት ጠሪዎችንና ሟርተኞን፣ የሚያነበንቡትንና የሚያሾከሹኩትን ጠይቁ ይላችኃል፤ ግን ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ የለበትምን›› ትምህርትና ምስክርነት ለማግኘት ለሕያዋን ሙታን መጠየቅ አለባቸውን? ወይም 2) ‹‹እነዚያን የሚያነበንቡትንና የሚያሾካሽኩትን መናፍስት ጠሪዎችን ሟርተኞች ጠይቁ ይሏችኃል፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ የለበትምን? ሕጉንና ምስክርነቱን በተመለከተ ለሕያዋን ሙታን መጠየቅ አለባቸውን?

እንዲህ ይሉሃል

‹‹እነርሱ›› የሚለው የሚያመለክተው በያህዌ የማይታመኑን ነው፡፡ ‹‹አንተ›› የሚለው በብዙ ቁጥር ነው፤ በያህዌ የሚታመኑትን ያመለክታል፡፡

መናፍስት ጠሪዎችንና ሟርተኞችን ጠይቁ

‹‹ምን ማድረግ እንዳለባችሁ መናፍስት ጠሪዎችንና ሟርተኞችን ጠይቁ››

መናፍስት ጠሪዎችና ሟርተኞች

ከሙታን ጋር እንነጋገራለን የሚሉ ሰዎች

የሚያነበንቡ

እንደ ወፍ ያለ ድምፅ የሚያወጡ

ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕይወት ስላሉትስ ሙታንን መጠየቅ አለባቸውን?

ባለ ማስተዋል ከሙታን ጋር ለመነጋገር ከመሞከር ይልቅ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን መጠየቅ እንዳለበት እነዚህ ጥያቄዎች ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲመራቸው ሕዝቡ ያህዌን መጠየቅ አለባቸው፤ ከሞቱ ሰዎች መልስ መፈለግ የለባቸውም››

ሕጉና ምስክሩ

ይህም ማለት 1) ‹‹የእግዚአብሔርን መመሪያና ትምህርት ልብ ብላችሁ አድምጡ›› ወይም 2) ‹‹ያኔ እኔ የሰጠሁትን ትምህርትና ምስክር ማስታወስ አለባችሁ›› (ኢሳይያስ 8፥16)

ሕጉ

ይህ ኢሳይያስ 8፥16 ላይ፣ ‹‹ሕጉ›› ተብሎ ከተተረጐመው ጋር አንድ ነው፡፡

ምስክሩ

ኢሳይያስ 8፥16 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት

እነርሱም እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ

‹‹ሕጉንና ምስክሩን ባይናገሩ››

የንጋት ብርሃን ስለሌላቸው ነው

እግዚአብሔርን የማያውቁ ምንም ብርሃን በሌለበት ጨለማ እንደሚመላለሱ ሰዎች እንደሆኑ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጨለማ እንደዋጠው ሰው ስለሆኑ ነው››