am_tn/isa/08/16.md

1.5 KiB

ምስክርነቴን አሸገው፤ ሕጉንም አትመው

እነዚህ ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፤ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በላዩ ይህን መልእክት ጽፈህ፣ ጥቅልል ጽሑፉን አጥብቀህ አሽገው››

ምስክርነቴ… ደቀ መዛሙርቴ

‹‹የእኔ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማንን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ኢሳይያስ ወይም ያህዌ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ቋንቋህ የሚፈቅድ ከሆነ ተውላጠ ስሙን አሻሚ እንደሆነ መተው ይመረጣል፡፡

ያህዌን እጠብቃለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እኔ›› የሚያመለክተው ኢሳይያስን ነው፡፡

ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሰወረውን

የያህዌ፣ ‹‹ፊት›› በረከቱንና ሞገሱን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከያዕቆብ ቤት በረከቱን የወሰደውን›› ወይም፣ ‹‹የያዕቆብን ቤት በሞገስ ማየት የተወውን››

የያዕቆብ ቤት

የእስራኤል ሕዝብ

እኔና ያህዌ የሰጠኝ ልጆቼ ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን

‹‹እኔና ያህዌ የሰጠን ልጆቼ የእስራኤልን ሕዝብ የምናስጠነቅቅ ምልክቶች ነን›› ልጆቹ ስሞቻቸው ለእስራኤል ሕዝበ መልእክት የሆኑት ሸአብ ያሹብ እና ማኽር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ናቸው፡፡