am_tn/isa/08/14.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ 8፥11-13 ላይ የጀመረውን ያህዌን ቀጥተኛ ባልሆነ ሁኔታ መጥቀሱን ኢሳይያስ ቀጥሏል፡፡ ያህዌ በመጀመሪያ ሰው ደረጃ እየተናገረ እንደሆነ በሚያመለክት ሁኔታ በቀጥታ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

እርሱ መቅደስ ይሆናል

‹‹መቅደስ›› የሚለው ቃል ያህዌ ሕዝቡን እንደሚጠብቅና ለእነርሱ እንደሚከላከል የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ወደ እርሱ ሲሄዱ፣ እርሱ ይጠብቃቸዋል››

የሚያደናቅፍ ድንጋይ፣ የሚያሰናክልም ዐለት ይሆናል

‹‹የሚያደናቅፍ ድንጋይ›› እና፣ ‹‹የሚያሰናክል ዐለት›› የተሰኙት ያህዌ ሕዝቡን እንደሚጐዳ የሚመለክቱ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶች፣ ‹‹የሚያደናቅፍ›› እና፣ ‹‹የሚያሰናክል›› የሚለውን፣ ‹‹የሚያሰናክል››እና፣ ‹‹የሚጥል›› በማለት ይተረጉሙታል፡፡ ሌሎች ደግሞ፣ ‹‹በደል›› እና፣ ‹‹መሰናከያ›› በማለት ይተረጉማሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰዎችን እግር እንደሚመታና እንደሚያሰናክል ድንጋይ፣ ሰዎችን አደናቅፎ እንደሚጥል ዐለት ያህዌ ሕዝቡን ይጐዳል››

ለኢየሩሳሌም ሕዝብም ወጥመድና አሽክላ ይሆናል

‹‹ወጥመድ›› እና፣ ‹‹አሽክላ›› የተሰኙት ቃሎች በአመዛኙ ተመሳሳይ ናቸው፤ ያህዌ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለመቅጣት ሲወስን ማምለጥ እንደማይችሉ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእርሱ ማምለጥ እንዳይችሉ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያጠምዳል››

ወጥመድ

ወፍን በመረብ ወይም በቅርጫት የሚይዝ ነገር

አሽክላ

የእንስሳን እግር ወይም አፍንጫ የሚይዝ ወጥመድ

ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ ይወድቃሉ፤ ይሰበራሉ፤ ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ፤ ይያዛሉም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙ ሰዎች በድንጋዩ ይሰናከላሉ፤ ከወደቁም አይነሡም፤ ብዙዎች አሽክላው ላይ ይቆማሉ፤ ከዚያ መውጣትም አይችሉም››

ይጠመዳሉ ይያዛሉም

እነዚህ ቃሎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፤ በወጥመድ እንደሚያዙ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡