am_tn/isa/08/11.md

1.6 KiB

ብርቱ እጁን በላዬ አድርጐ ያህዌ ተናገረኝ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ብርቱ እጁን በላዬ አድርጐ›› የሚለው የያህዌን ኀይል የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ በጣም ብርቱ በሆነ መንገድ ተናገረኝ››

በዚህ ሕዝብ መንገድ እንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ

ይህ 8፥17 የሚደመደምበት ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንዲህ ሲል አስጠነቀቀኝ፤ ‹ይህ ሕዝብ የሚያደርገውን አታድርግ››

እነዚህ ሰዎች አድማ ነው የሚሉትን ማንኛውንምነገር አድማ አትበል

ሰዎች አድማ መኖሩን ስለሚያስቡ ስጋት አድሮባቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁሌም እነርሱ መጉዳት የሚፈልግ ሰው እንዳለ እንደሚገምቱት እንደ እነዚህ ሰዎች አትጨነቅ››

ልትቀድሱ የሚገባው የሰራዊት ጌታ ያህዌን ብቻ ነው፤ ልትፈሩት የሚገባው እርሱን ነው፤ ልትንቀጠቀጡለት የሚገባውም እርሱ ነው፡፡

ይህን በቀጥተኛ ጥቅስ የምትተረጉም ከሆነ፣ ያህዌ በመጀመሪያ ሰው ደረጃ እየተናገረ መሆኑንም መተርጐም ይኖርብሃል፤ ‹‹ነገር ግን እኔን የሰራዊት ጌታ ያህዌን ልትቀድሱኝ ይገባል፣ እኔን መፍራትና በፊቴም መደንገጥ አለባችሁ››