am_tn/isa/08/05.md

1.9 KiB

ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈሰስውን የሰሊሆምን ውሆች ስለ ተወ

‹‹በጸጥታ የሚሄደው›› የተባለው የሚያመለክተው የጌታን ሕግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ ሕዝብ እንደ ሰሊሆም ውሆች በጸጥታ የሚሄደውን የያህዌን ሕግ ስለ ተወ››

ይህ ሕዝብ

‹‹ይህ ሕዝብ ሁሉ›› እዚህ ላይ ቋንቋህ ብዙ ቁጥር የሚፈልግ ከሆነ፣ ‹‹እነዚህ ሕዝቦች ስለ ተው… ደስተኛ ናቸው›› በማለት ይህን ሐረግና የሚከተለውን ግሥ መተርጐም ይቻላል፡፡

በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቶአልና

ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ ኢሳይያስ 7፥1 ላይ የእነዚህን ሰዎች ስም እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአሦር ሰራዊት የሶርያን ንጉሥ ረኦሶንንና የሮሜልዮን ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔን ድል ስላደረገ ተደስቶአል››

ስለዚህ ጌታ

ስለ ማንነቱ ለሕዝቡ ለማሳሰብ ያህዌ እርሱ ሌላ ሰው ይመስል ስለ ራሱ እየተናገረ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ እኔ ያህዌ…››

ያመጣባቸዋል

ግሡ፣ ‹‹ያመጣባቸዋል››፤ ተውሳከ ግሡ፣ ‹‹እነርሱ ላይ››

እነርሱ ላይ

‹‹የይሁዳ ሕዝብ ላይ››

ታላቁንና ብርቱውን የጐርፍ ውሃ፤ የአሦር ንጉሥ ከነግርማ ሞገሱ

ወንዙ የሚወክለው የአሦርን ሰራዊት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ታላቅና ብርቱ ጐርፍ የሆነው ከአሦር የሚመጣው ሰራዊት››

ወንዙ

በአሦር ያለው የኤፍራጥስ ወንዝ